የወር አበባ (Menstrual Cycle)
Apr 21, 2025
ተፈጥሮአዊ የወር አበባ ዑደት የሚባለው (Regular menstrual cycle)
አቆጣጠሩ፣ የወር አበባ የመጣበት የመጀመሪያ ቀን እስከ የሚቀጥለው የወር አበባ የመጣበት ቀን ሲሆን፣ የወር አበባ በየ 21 እስከ 35 ቀን የሚመጣ ሲሆን ፍሰቱ ከሁለት እስከ ሰባት ቀን ይቆያል።
የወር አበባሽ ላይ ችግሮች እንዳሉ ለማወቅ፡ ከታች የተዘረዘሩትን በየወሩ መዝግበሽ ተከታተይ፡
- የወር አበባ የሚመጣበትን ቀን
- ከተለመደው ፈሳሽ መጠን በጣም ይበዛል ወይስ በጣም ያንሳል?
- ከተለመደው የወር አበባ ዑደትሽ ውጭ በየመሃሉ ይመጣል?
- ከተለመደው ጊዜው የበለጠ የህመም ስሜት አለሽ?
- ከወትሮ የተለየ የባህሪ ወይም የስሜት ለውጥ አለሽ?
የወር አበባ በምን ምክንያቶች ሊዛባ ወይም ሊቀር ይችላል?
- በእርግዝና ወቅት ወይም ጡት በምታጠቢበት ጊዜ መቅረት (ተፈጥሮአዊ ነው)
- የአመጋገብ ስራዓት ሲዛባ
- ከመጠን በላይ ውፍረት ወይም ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ
- ከባድ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ሆርሞናል የእርግዝና መከላከይ መጠቀም
- የሆርሞን መዛባት
- ጭንቀት
- የማህጸን ኢንፌክሽን
- የማህጸን እጢ
- ፖሊሲስቲክ ኦቫሪያን ሲንድረም (PCOS)
- ከ40 አመት በፊት የእንቁላል መምረቻ ስርዓት ሲዛባ (POF)
- ወደ ማረጥ የእድሜ ደረጃ ሲደረስ
ከታች የተዘረዘሩትን መልክቶች ስታይ፡ ሃኪምሽን ማማከር ይኖርብሻል (irregular menstrual cycle)
- የወር አበባ ዑደትሽ ከ21 ቀን ሲያንስ ወይም ከ 35 ቀን ሲበልጥ
- የወር አበባሽ ድንገት ለሶስት ወር እና ካዚያ በላይ ወራቶች ሲቀር (Amenorrhea)
- የወር አበባሽ ከተለመደው መጠን በብዛት ሲፈስሽ እና ከ7 ቀናት በላይ ሲፈስሽ (Menorrhagia)
- የወር አበባሽ ቶሎ ቶሎ መምጣት ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው (polymenorrhea)
- የወር አበባሽ ከተለመደው የፍሰት መጠን በጣም ሲያንስ (Hypomenorrhea)
- በወር አበባ ዑደትሽ ሳይደርስ በመሃል ሲፈስሽ (Intermenstrual bleeding)
- የወር አበባሽ በሚፈስ ወቅት ከባድ ህመምሲኖርሽ (Dysmenorrhea)