እርግዝና ስታስቢ፡ ማወቅ ያለብሽ የቅድመ እርግዝና ዝግጅቶች
Apr 21, 2025
በአደጉ አገሮች ጭምር እስከ 50% ያልታቀደ እርግዝና ይፈጥራል።
እርግዝና እንዲፈጠር ስታቅጅ፣ ጤናማ የሆነ ጽንስ እንዲፈጠር፣ የሚያስፈልጉሽ የቅድመ እርግዝና ዝግጅቶች፤
- ቢያንስ እርግዝና ከመሞከርሽ ከሁለት ወር በፊት ( 0.4mg እስከ 0.8mg ) ፎሊክ አሲድ በየቀኑ መወሰድ፣ በጽንሱ አፈጣጠር ላይ ችግር እንዳይኖር ይረዳል።
- ጤናማ ምግቦችን መመገብ
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- የጥርስ ንጽህናን መጠበቅ
- መጠነኛ የሆን የሰውነት ክብደት ላይ መሆን ይኖርብሻል (ከበቂ ክብደት በታችም ወይም ከበቂ ክብደት በላይ መሆን የለብሽም)
- አንችንና ጽንሱን ከሚጎዱ ነገሮች መራቅ፡ እንደ ( ሲጋራና ሽሻ ማጨስ፡ ከልኮል መጠጣት፡ አደንዛዥ እጽ መጠቀም እና ሌሎች አነቃቂ መድሃኒቶች መውሰድ )
- በሃኪም ያልታዘዙ መድሃኒቶችን ከመውሰድ በፊት ሃኪምሽን ማማከር
- በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎችን ኤች አይ ቪን ጨምሮ ምርመራ ማድረግ እንዱሁም የሄፒታይተስ B እና C ምርመራ ምድረግ
- የደም አይንት መርመራ ማድረግ
- ከዚህ በፊት የሚታወቁ በሽታዎችን ለሃኪምሽ ማሳውቅ፡ እንደ ( የአስም፡ የስኳር ፡ የልብና የታይሮይድ በሽታውችን )
- ከዚህ በፊት እርግዛና ላይ ያጋጠሙሽ ችግር ካሉ ለሃኪምሽ ማማከር፡ እንደ (የአፈጣጠር ችግር፡ ቀኑ ሳይደርስ መውለድ፡ በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የደም ግፊት፡ ስኳር፡ በወሊድ ጊዜ የሚያጋጥም የደም መፍሰስ፡ በእርግዝና ጊዜ የደም መርጋት )
እርግዝና ስታስቢ በትንሹ ከ ሶስት ወር ቀደም ብለሽ ከሃኪምሽ ጋር የቅድመ እርግዝና ምርመራዎችና ምክር አገልግሎት መውሰድ፡ ጤናማ ልጅ እንዲኖሽ ይረዳል፡፡