የማህጸን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ
Apr 21, 2025
የማህጸን በር ካንሰር፡ ዋነኛ መንስኤ በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) አማካኝነት ሲሆን፡ በግብረስጋ ግንኙነት ከአንዱ ወደ ሌላው ይተላለፋል፡፡
በአደጉ አገሮች የቅድመ ካንሰር ምርመራና ልየታ በማድረግ፡ የማህጸን በር ካንሰር በሽታን ወደ ካንሰርነት ከመቀየሩና የከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ህክምና በማድረግ በዚህ የካንሰር በሽታ የሚሞተውን ሰው ቁጥር በ70% ቀንሰዋል፡፡
በአገራችን በበቂ ሁኔት የማህጸን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ ሰለማይደረግ በበሽታው የሚሞት ሰው ብዙ ነው፡፡
ቅድመ ምርመራ
አንደ ሴት እድሜዋ ከ 30 እስከ 65 ዓመት ወስጥ ከሆነች በየ 3 አመቱ የቅድመ ካንሰር ምርመራ (Pap smear) ማድረግ ይኖርባታል፡፡
ምርመራ ለማድረግ፣ ለ48 ሰዓት የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፤
- ከግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ ይኖርባታል
- የወር አበባ ላይ መሆን የለባትም
- ውሃ ወደ ማህፀን አስገብቶ መታጠብ የለባትም
- ወደ ማህጸን የሚገባ ምንም አይነት መድሃኒት መውሰድ የለባትም